ነፃ የበጋ ምግብ

በዚህ የክረምት ወቅት ለህጻናት እና ለወጣቶች ነጻ ምግቦች በመኖሪያ አካባቢዎ ይቀርባሉ። ነፃ የክረምት ምግቦች ፕሮግራሞች ቤተሰብዎ በሚኖሩበት፣ በሚማሩበትና በሚጫወቱባቸው ቦታዎች—ትምህርት ቤቶችን፣ መናፈሻዎችን፣ የማህበረሰብ ማእከላት እና እምነትን መሰረት ያደረጉ ድርጅቶችን ጨምሮ ባሉ ቦታዎች ይቀርባሉ።

ነፃ የክረምት ምግቦች ፕሮግራሞች ለሁሉም ቤተሰቦች ክፍት ሲሆኑ ምንም አይነት የወረቀት ስራ አይጠይቁሙ—ልጆች ዝም ብለው ገብተው ምግብ መውሰድ ይችላሉ። ብዙ ድህረ-ገጾችም ልጆች ትምህርት ቤት ሲዘጋ ንቁ ሆነው እንዲቆዩ የሚያግዙ አስደሳች ተግባራትን ያቀርባሉ።

ከዚህ በታች በአካባቢዎ ወደ እሚገኘው ነፃ የክረምት ምግቦች ጣቢያ ይሂዱ እና በዚህ ክረመት በማህበረሰብዎ ውስጥ ያሉ ሌሎች የምግብ ምንጮችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ይወቁ።


አሁኑኑ ምግብ ያግኙ


ምግብ ለ ልጆች

ነፃ የክርመት ምግቦች ለልጆችና ታዳጊ ወጣቶች በፓርኮች፣ በማህበረሰብ ማዕከላት፣ በትምህርት ቤቶች እና በማህበረሰብዎ ውስጥ ባሉ እምነት ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች ውስጥ ይቀርባሉ። በዚህ አመት ስለ ነፃ የክረምት ምግቦች ማወቅ ያለብዎት ጥቂት ጠቃሚ ነገሮች፦

  • የህ ነጻ የክረምት ምግቦች ፕሮግራሙ እድሜያቸው 18 እና ከዚያ በታች ለሆኑ ልጆች እና ታዳጊዎች ነው የሚቀርበው—ነገር ግን አንዳንድ ጣቢያዎች ለትላልቅ የቤተሰብ አባላትም ተጨማሪ ግብዓቶችን ሊሰጡ ይችላሉ።
  • የክረምት ምግቦችን ለመቀበል ምንም ክፍያ፣ ምዝገባ ወይም የማንነት ማረጋገጫ አሊያም ህጋዊ ሁኔታ አያስፈልግም።
  • የፌዴራል ፕሮግራም ደንቦች ተለውጠዋል። በዚህ አመት ልጆችና ታዳጊዎች በቦታው/ጣብያው ላይ ተገኝተው ምግባቸውን በመቀበል እዛው ምግባቸውን መመገብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ በኋላ ወላጆችና አሳዳጊዎች በልጆቻቸው ስም ምግብ መውሰድ አይችሉም።

በአቅራቢያዎ ያሉ የምግብ ጣቢያዎችን ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው ካርታ ላይ አድራሻዎን ያስገቡ ወይም ወደ 304-304 FOOD ብለው የፅሁፍ መልእክት ይላኩ፦