ነጻ የግብር እርዳታ ያግኙ

አስተማማኝ፣ ምቹ፣ ቀላል እና ነጻ የግብር እርዳታ

ተግተው ያገኟቸውን ዶላሮች የበለጠ ይቆጥቡ እና የ2020 ዓ.ም ግብርዎን ለመሙላት በነጻ እርዳታ ያግኙ።

ከጥር 20 እስከ ሚያዚያ 18, 2021 ዓ.ም ድረስ የሰለጠኑ እና የሃገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት (IRS)-ማረጋገጫ ያገኙ የግብር ኤክስፐርቶች አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በግብር አሞላልዎ ላይ 100% የኦንላይን እገዛ ሊያደርጉልዎ ዝግጁ ናቸው። ኤክስፐርቶቻችን አዲሱን የማቋቋሚያ ክፍያ ጨምሮ ስለ ሁሉም አዲስ የግብር ህጎች እና ስለሚቀርቡ ብድሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆኑ የግብር ተመላሽን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሳድጉ ማድረግ እና የበለጠ ገንዘብዎን ይዘው እንዲቀጥሉ ማድረግ ይችላሉ። በተንቀሳቃሽ የቼክ ገንዘብ ላይም ልንረዳዎ እንችላለን።

 ነጻ የግብር እርዳታ በተጨማሪም የግለሰብ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ITIN) ያዦችን ጨምሮ ለሁሉም ሰው ይቀርባል።

በግብርዎ ላይ በጥሩ ሁኔታ እንድንረዳዎ የሚያስፈልጉዎ አንዳንድ ነገሮች እንዲሁም መሰብሰብ እና ማቅረብ ያሉብዎ ተጨማሪ አማራጭ ሆኖም ጠቃሚ ሰነዶች እዚህ ላይ ተገልፀዋል፡

ምን እንደሚያስፈልግዎ

  • ፎቶ የያዘ የመታወቂያ ካርድ
  • ፊትዎን አቅርበው እራስዎን ያነሱት ፎቶዎን የያዘ የመታወቂያ ካርድ
  • የማህበራዊ ዋስትና ካርድ ወይም የITIN ሰነድ
  • የትኛውም የገቢ ሰነዶች (W-2, 1099-R፣ ወዘተ)

በአማራጭነት መቅረብ ያለባቸው ሌሎች ሰነዶች

  • ያለፈው አመት የግብር ተመላሽ
  • የጤና መድን ዋስትና የገበያ ቦታ መግለጫ (1095-A)
  • የህጻን እንክብካቤ መግለጫ
  • የአቋማሪ ማስጠንቀቂያዎች መግለጫ
  • የትምህርት ክፍያ መግለጫ

ግብሮችን በነጻ ማስመዝገቢያ ቀላል ዘዴዎች


የሚረዳዎ ሰው ያግኙ

GetYourRefund.org

ነጻ የግብር ዝግጅት አገልግሎቶችን በኦንላይን ያግኙ በIRS-ማረጋገጫ ያገኙ የግብር ኤክስፐርቶች ከእርስዎ ጋር አብረው በመስራት በርቀት ሆነው የእርስዎን የግብር ተመላሽ አዘጋጅተው ስለ እርስዎ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ያስመዘግባሉ። አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፖርታል ተገቢ ሰነዶችዎን መጫንን ቀላል ያደርግልዎታል።

በራስዎ ያስመዝግቡ

MyFreeTaxes.com

MyFreeTaxes.comን በመጠቀም ግብርዎን በራስዎ በነጻ ማስመዝገብ ይችላሉ። ይህ አገልግሎት የግል መረጃዎን እንዲፈጥሩ፣ ግብሮችዎን በራስዎ እንዲመዘግቡና እንዲያስገቡ ይጠይቅዎታል።

እገዛ ለማግኘት ይደውሉ

2-1-1

ግብሮችዎን እንዴት በነጻ እንደሚያስመዘግቡ እርዳታ ማግኘትን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች መረጃና እገዛ ለማግኘት በ 2-1-1 to መደወል ይችላሉ።


የተለመዱ ለMyFreeTaxes.com የሚቀርቡ ጥያቄዎች


ቀላል ተመላሽ ምንድን ነው?

በMyFreeTaxes የሚሸፈኑ ቀላል የግብር ተመላሾች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ: የW-2 ገቢ፣ የውሱን ገቢ ወለድ፣ የተከፋይ ገቢ፣ የተማሪ የትምህርት ወጪዎች፣ የሥራ አጥነት ገቢ፣ የተማሪ የትምህርት ብድሮች፣ የተማሪ የብድር ወለድ፣ መደበኛ ትምህርት መጠየቂያ፣ የተገኘ ገቢ የግብር እዳዎች፣ የህጻናት ግብር እዳ፣ እና የህጻናትና ጥገኞች እንክብካቤ ወጪዎች። የተካተቱ ቅጾች ሙሉ ዝርዝርን እዚህ ላይ ከ፡ MyFreeTaxes.com/Support ማግኘት ይቻላል።

የአገልግሎቶቹ ገደቦች ምንድን ናቸው?

በዋናነት በይዘት አድማስ ውስጥ የሚካተቱ እና በአካል የግብር መክፈያ ቦታዎቻችን በነጻ የሚቀርቡ የትኛውም ተመላሾች በነጻ ሶፍትዌሩ ውስጥ አይካተቱም፤ ለምሳሌ፡ ከግል ስራ የሚገኝ ገቢ (1099-MISC)፣ የቤት ብድር ወለድ፣ የሪል ስቴት ግብሮች፣ ሌሎች በዝርዝር የቀረቡ ተቀናሾች፣ የሶስተኛ ወገን ክፍያዎች (1099-K)፣ HSA፣ እና ሌሎችም።  እነዚህ የግብር ቅጾች ካሉዎ እነዚህን በሲስተሙ ላይ ለማስመዝገብ የደረጃ ማሻሻያ መግዛት ይኖርብዎታል። ሆኖም MyFreeTaxes.comን የሚጠቀሙ ከሆነ ቅናሽ ያገኛሉ። በነጻ ሶፍትዌሩ ስር ምን እንደሚካተት የተመለከተ የተሟላ ዝርዝር ከ MyFreeTaxes.com/Support ላይ ማግኘት ይቻላል።

የማገኛቸው ሌሎች ነጻ ምንጮች/አገልግሎቶች ምንድን ናቸው?

ጥቂት የተለያዩ አማራጮችን ማጥናት ይችላሉ:

  • በኤክስፐርቶቻችን የሚደረግ ነጻ የቨርቹዋል የግብር ዝግጅት: ግብሮችዎን በነጻ የግብር ዝግጅት የኤክስፐርት ቡድናችን አማካኝነት እንዲዘጋጁ ያድርጉ። ተጨማሪ መረጃ org አማ ላይ ለማግኘት ይህን ገጽ ወደ ታች ያንቀሳቅሱ።
  • በኦንላይን ማስመዝገብ: ተጨማሪ የነጻ ማስመዝገቢያ መሳሪያዎችን በIRS Free File/ነጻ የማስመዝገቢያ ፕሮግራሞች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃና ዝርዝሮችን ለማግኘት gov/FreeFile የሚለውን ድረገጽ ይጎብኙ።

በMyFreeTaxes.com ላይ ለማስመዝገብ ምን ማድረግ አለብኝ?

የሚከተሉት ያስፈልጉዎታል:

  • የግል መረጃ ለመፍጠር የሚያገለግል የኢሜይል አድራሻ
  • ከ 2019 ዓ.ም የግብር ተመላሽዎ ቅጽ 1040 መስመር 7 ላይ የተወሰደ ትክክለኛ AGIዎ (ማንነትዎን ለማረጋገጥ የሚያገለግል)
  • በተመላሹ ላይ የተገለጸ የእያንዳንዱ ሰው SSN
  • ሁሉም የግብር ሰነዶች
  • የባንክ ሂሳብ እና የማግኛ መስመር ቁጥር (ለቀጥተኛ ተቀማጭ/ዴቢት)

የ 2019 ዓ.ም AGIዬን አላውቀውም። ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

ይህን የተመላሽዎ ኮፒ አሁንም በእጅዎ ላይ የሚገኝ ከሆነ ከ 2019 ዓ.ም ተመላሽዎ መስመር 7 ላይ ማግኘት ይችላሉ። ባለፈው አመት ግብሮችዎን ያስመዘገቡት በ United Way of King County ነጻ የግብር ዝግጅት ቦታ ከሆነ በ freetax@uwkc.org የኢሜይል መልዕክት ይላኩ እንዲሁም ያለፈው አመት ተመላሽዎን ኮፒ ለእርስወዎ ለመስጠት እንዲያስችለን የስልክ ቁጥርዎን ያካቱ። ባለፈው አመት ያስመዘገቡት እኛ ጋር ካልሆነ IRS.gov/get-transcript ያለፈውን አመት የግብር ተመላሽዎን ኮፒውን እንዲያገኙ ሊረዳዎ ይችላል።

ተመላሼን ደረጃ በደረጃ በምሞላበት ወቅት የተወሰነ ሰው በዚህ ላይ በስልክ ሊረዳኝ ይችላል?

ድጋፍ ወይም እገዛ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ የግብር ተመላሽዎን ቀጠሮን መሰረት ባደረገ ሲስተማችን አማካኝነት በአካባቢ ነጻ የግብር ዝግጅት የኤክስፐርት ቡድናችን በቨርቹዋል ማስሞላት ይችላሉ፤ ተጨማሪ መረጃ GetYourRefund.org አማራጭ ላይ ለማግኘት ይህን ገጽ ወደ ታች ያንቀሳቅሱ።

የ United Way of King County የተወሰነ ሰው መረጃዬን እኔን ወክሎ በMyFreeTaxes.com ላይ ሊያስገባልኝ ይችላል?

ከይቅርታ ጋር የ United Way of King County እርስዎን ወክሎ መረጃዎን እና የግብር ሰነዶችዎን ወደ MyFreeTaxes.com ሊያስገባልዎ አይችልም። ግብሮችዎ ቀጠሮን መሰረት ባደረገ ሲስተማችን አማካኝነት በአካባቢ ነጻ የግብር ዝግጅት የኤክስፐርት ቡድናችን በቨርቹዋል እንዲዘጋጁልዎ የሚፈልጉ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ ከ GetYourRefund.org አማራጭ ላይ ለማግኘት ይህን ገጽ ወደ ታች ያንቀሳቅሱ።

ለIRS.gov/FreeFile ብቁ ነኝ?

ማንኛውም ገቢው ከ$72,000 በታች የሆነ ሰው የIRS Free File/ነጻ የማስመዝገቢያ ፕሮግራሞችን በመጠቀም በነጻ ማስመዝገብ ይችላል።


የተለመዱ ለGetYourRefund.org የሚቀርቡ ጥያቄዎች


GetYourRefund.org የሚሰራው እንዴት ነው?

GetYourRefund.org የግብር ተመላሽዎን ጥቂት ቀላል ደረጃዎችን በመጠቀም በቨርቹዋል የሚሞሉበትን ዘዴ ያቀርብልዎታል:

  1. ለነጻ የቨርቹዋል የግብር ዝግጅት በ “File with GetYourRefund/ከ GetYourRefund ዘንድ ያስመዝግቡ” ላይ ይጫኑ።
  2. የGetYourRefund የግል መረጃዎን ይፍጠሩ፣ የቅበላ ጥያቄዎችን ይመልሱ እንዲሁም የግብር ሰነዶችዎን ፎቶዎች ይጫኑ።
  3. የቀጠሮ የጊዜ ሰሌዳ ያስይዙ።
  4. በቀጠሮዎ ወቅት:
  • ከግብር ኤክስፐርቶቻችን መካከል ከአንዱ የቅበላ የስልክ ጥሪ ይደርሱዎታል።
  • ከግብር ኤክስፐርቶቻችን መካከል ከአንዱ የቅበላ የስልክ ጥሪ ይደርሱዎታል።
  • ተመላሽዎን መርምሮ ሞልቶ ለማጠናቀቅ በድጋሚ ከግብር ኤክስፐርቶቻችን መካከል ከአንዱ የስልክ ጥሪ ይደርስዎታል።
  1. የተሞላውን ተመላሽዎን በኢሜይል ይፈርሙ።

በዚህ አገልግሎት ላይ የተቀመጡ ገደቦች ምንድን ናቸው?

United Way እኩል እድል የሚሰጥ አቅራቢ በመሆኑ በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው የUnited Wayን ነጻ የግብር ዝግጅት አገልግሎቶች ማግኘት ይችላል። ሆኖም አንዳንድ ተመላሾች ለበጎ ፍቃደኞቻችን እጅግ ውስብስብ ናቸው። ለምሳሌ፡ በሌሎች ግዛቶች የተገኘ ገቢ ተመላሾችን ማዘጋጀት አንችልም።

 

ተመላሾችን በITIN ለማስተናገድ ከExpress Credit Union ጋር በትብብር የምንሰራ ከመሆኑም በተጨማሪ በExpress Credit Union በኩል ነጻ የITIN ማመልከቻዎች እና እድሳቶችን እናቀርባለን።

 

የማናቀርባቸው አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው:

  • የግዛት ተመላሾች (የዋሽግተን ግዛት የትኛውም የግዛት የገቢ ግብር የሌለው በመሆኑ ምክንያት ምንም ተመላሽ አያስፈልግም። የሰሩት የግዛት ተመላሽ በሚጠየቅበት ግዛት ውስጥ ከሆነ በነጻ ለማስመዝገብ com ን መጠቀም ይችላሉ)።
  • 1099-B (ከድለላ ያገኟቸው ገቢዎች፣ የስቶክ ግዢ/ሽያጭ) ካሉዎት።
  • መኖሪያ ቤትዎን ከሸጡ ወይም ቤቱ በብድር ማስያዣ ከተወሰደ።
  • የኪራይ ገቢ ተቀብለው ከሆነ።
  • የግል ስራዎን የሚሰሩ ከሆነ እና ከ$25,000 በላይ ወጪዎች ካሉብዎ፣ የተጣራ ኪሳራ ካሉዎ ወይም መኖሪያ ቤትዎን መጠቀምዎን እንደ ስራ ወጪ አድርገው መቀነስ ከፈለጉ።
  • የተመዘገቡ የሀገር ውስጥ የሽርክና ማህበር ከሆኑ።

በGetYourRefund.org ላይ ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉዎ ምንድን ነው?

GetYourRefund.org በሞባይል ስልኮች፣ ታብሌቶችና ዴስክቶፖች ይገኛል። ለአብዛኞቹ ሰዎች ጥያቄዎቹን መሙላት እና በቅበላ አማካኝነት ማግኘት በንጽጽር ቀላል ሆኖላቸው አግኝተነዋል። የሚከተሉት ያስፈልጉዎታል:

  • የግል መረጃ ለመፍጠር የሚያገለግል የኢሜይል አድራሻ
  • ፎቶ የያዘ የመታወቂያ ካርድ (እና በተጨማሪ በተመላሹ ላይ የተገለጸ የትኛውም ሌላ ሰው)
  • የመታወቂያ ካርድዎን የያዘ የራስዎ ፎቶ
  • የማህበራዊ ዋስትና ወይም የITIN ካርድ (እና በተጨማሪ በተመላሹ ላይ የተገለጸ የትኛውም ሌላ ሰው)
  • ሁሉም የግብር ሰነዶች
  • የባንክ ሂሳብ እና የማግኛ መስመር ቁጥር (በአማራጭነት፣ ለቀጥተኛ ተቀማጭ/ዴቢት)

 

እባክዎ ልብ ይበሉ: IRS፣ GetYourRefund.org፣ የ United Way of King County እና ብሔራዊ አጋሮች በዋስትና አሰራሮች እና በቨርቹዋል የግብር ዝግጅት መስፈርቶች ላይ መሰረታዊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።

በ GetYourRefund.org እገዛ ማግኘት ብፈልግ እንዴት እርዳታ ማግኘት እችላለሁ?

በዚህ ገጽ ላይ ለጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የ United Way of King County የደንበኞች ድጋፍ ሰራተኞችን ማግኘት የሚቻልበት የመወያያ አገልግሎት/መተግበሪያ አለ።

 

በዚህ ድረገጽ ላይ የሚገኘው የመወያያ አይከን/ምልክትን ይጫኑና እርዳታ የሚያደርግልዎ የተወሰነ ሰው ማግኘት ይችላሉ።

 

በተጨማሪም በ GetYourRefund.org ድረገጽ መተግበሪያ ላይ ለማግኘት የሚቻሉ የደንበኞች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አሉሉ። በተጨመማሪም ተጨማሪ እገዛ ለማግኘት ለ Hello@GetYourRefund.org የኢሜይል መልዕክት መላክ ይችላሉ።

የክፍያዎች ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ምንድን ነው?

በኮሮና ቫይረስ የእርዳታ፣ የበጎ አድራጎት እርዳታና የኢኮኖሚ ዋስትና/ Coronavirus Aid, Relief, and Economic Security/ የኮሮቫይረስ የእርዳታ፣ የእፎይታ እና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት (CARES) ህግ ስር ለ 2019 ወይም 2018 ዓ.ም የግብር ተመላሾችን ያስመዘገቡ ብቁ የሆኑ ግብር ከፋዮች በአፋጣኝ ለግለሰቦች እስከ $1,200 ወይም ለተጋቡ ጥንዶች እስከ $2,400 እና ለእያንዳንዱ ብቁ ህጻን እስከ $500 የኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ክፍያ ያገኛሉ። በዋናነት ተመላሾችን የማያስመዘግቡ አንዳንድ ግብር ከፋዮች የኢኮኖሚ ተጽእኖ ክፍቸያ ለማግኘት ቀላል የግብር ተመላሽ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 

ተጨማሪ የኢኮኖሚ ተጽእኖ ክፍያ ከ 2021 ዓ.ም መግቢያ ጀምሮ ለግለሰቦች እስከ $600 ወይም ለተጋቢ ጥንዶች እስከ $1,200 እና ለእያንዳንዱ ብቁ ህጻን እስከ $600 ተከፋፍሏል። ቅልቅል ደረጃ ያላቸው ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት ለሁለቱም የኢኮኖሚ ተጽእኖ ክፍያዎች ብቁ ናቸው።

 

የቅርብ መረጃዎችን ለማግኘት IRS.gov/EIP ን ይጎብኙ።

 

የባንክ መረጃዎ ላይ ወቅታዊ ማሻሻያ ለማድረግ ወይም የኢኮኖሚ ተጽእኖ ክፍያዎ የደረሰበትን ደረጃ ለማረጋገጥ ይፈልጋሉ? ወደ IRS.gov/coronavirus/get-my-payment ይግቡ


ስለ ስፖንሰሮቻችን እናመሰግንዎታለን: