ለምግብ ተጨማሪ ገንዘብ ያግኙ

English, Español, እንግሊዘኛ, 中文, 영어, ວັນນະໂຣກ, Русский, Somali, Tiếng Việt

መሠረታዊ ምግብን (Supplemental Nutrition Assistance Program, SNAP, SNAP) መቀበል እንደ የህዝብ ክፍያ ደንብ አካል ተደርጎ አይቆጠርም፣ በስደተኝነት ሁኔታዎ ላይ ደግሞ ተጽዕኖ አያሳድርም። የተደባለቀ ሁኔታ ያላቸው ቤተሰቦች ሁልጊዜ ብቁ በሆኑ ልጆች ስም ማመልከት ይችላሉ። ለማመልከት በ 1-888-4FoodWA ይደውሉ።


ተጨማሪ ምግብ። አነስተኛ ጭንቀት። ቤዚክ ፉድ (Basic Food) (Basic Food) ጤናማ ምግብን በጠረጴዛ ላይ ለማስቀመጥ የሚረዳ ለአስቤዛ የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ነው።

እርስዎ ወይም ቤተሰብዎ አስቤዛዎችን ለመግዛት ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ለእርስዎ ጠቃሚ ነው። ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ምንድነው? SNAP (የተጨማሪ ምግብ አቅርቦት ድጋፍ ፕሮግራም) በመባል የሚታወቀው ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ዋሽንግተናውያን ምግብ ለመግዛት ወርሃዊ ጥቅሞችን እንዲያገኙ በማድረግ ይረዳል። አራት ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ $600 በወር ይቀበላል።

ቤዚክ ፉድ (Basic Food) የሚሰራው እንደሚከተለው ነው፡

  • በየወሩ የቤዚክ ፉድ (Basic Food) ዶላር ወደ EBT ካርድ ይገባል። 
  • የእርስዎ ቤዚክ ፉድ (Basic Food) EBT ካርድ በአስቤዛ ሱቆች፣ መስመር ላይ እና በብዙ የገበሬ ገበያዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው።
  • እንዲሁም ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ለተጨማሪ ጥቅሞች ብቁ ያደርግዎታል።:
    • ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ባላቸው ቤተሰቦች ውስጥ ያሉ ልጆች በነፃ የትምህርት ቤት ምግቦች ውስጥ ይመዘገባሉ፣ ማመልከቻ አያስፈልጋቸውም!
    • ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ባላቸው ቤተሰቦች ውስጥ ያሉ አዲስ የተወለዱ ጨቅላዎች እና ህጻናት ለሴቶች ጨቅላዎች እና ህፃናት (Women Infants and Children (WIC)) ፕሮግራም ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
    • ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ያላቸው የማህበረሰብ እና የቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች ለህፃናት እንክብካቤ ድጎማዎች፣ ለመፃህፍት፣ ለአስጠኚ ድጋፎች እና ለተጨማሪ ስኮላርሺፕ ሊረዳ ለሚችል ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) እና ሥራ ቅጥር ሥልጠና (Employment Training (BFET)) ፕሮግራም የትምህርትና የሥራ ስልጠና ፕሮግራም ብቁ ናቸው። 

ሌሎች ሰዎች መሰረታዊ ምግብ (Basic Food) እንዲያገኙ ለመርዳት ፍላጎት አለዎት? የሚሰሩት ለመሰረታዊ ምግብ ብቁ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር ነው? እዚህ ለማጋራት በራሪ ወረቀቶችን ያውርዱ፥ Basic Food Flyers.zip.


ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ብቁ የሆነው ማነው?


የሚከተሉት ቤተሰቦች እና ግለሰቦች…

  • ሥራ ያላቸው ወይም ሥራ አጦች
  • ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ወይም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች
  • ዜጎች ወይም የተደባለቀ የስደተኛ ጉዳዮች ያላቸው ቤተሰቦች

…ሁሉም ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ጥቅሞች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

እርስዎ ወይም ቤተሰብዎ አስቤዛዎችን ለመግዛት ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ ቤዚክ ፉድ (Basic Food) ለእርስዎ ጠቃሚ ነው።

የቤተሰብ መጠን፣ ጠቅላላ ገቢ (ቅድመ ግብር ገቢ)፣ እንዲሁም እንደ ቤት፣ መገልገያዎች እና የህክምና ወጪዎች ያሉ አንዳንድ ወጭዎች ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ብቁነትዎን ይወስናሉ። ለበለጠ መረጃ የአጠቃላይ ገቢ መመሪያዎችን ይመልከቱ።

እንደ ቤት፣ መኪና ወይም በባንክ ውስጥ ያለ ገንዘብ ያሉ ሀብቶች ብቁ እንዳይሆኑ አያደርጉም።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሁሉም የቤዚክ ፉድ (Basic Food) ተሳታፊዎች ለከፍተኛ ጥቅሞች ብቁ ናቸው። ይህ ማለት ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ብቁ የሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ በወር ቢያንስ $204 ይቀበላል ማለት ነው። ዛሬ ያመልክቱ!

የአጠቃላይ ገቢ መመሪያዎች
(4/1/2020 – 3/31/2021)

Family Sizeጠቅላላ ወርሀዊ ገቢ
1 ሰው$2,147
2$2,903
3$3,660
4$4,417
5$5,173
6$5,930
10+እያንዳንዱ $756

ለማመልከት የሚያስፈልግዎ ነገር


ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ከማመልከትዎ በፊት የሚያስፈልግዎት ነገሮች እዚህ አሉ፡

  • ካለፉት 30 ቀናት ጀምሮ የገቢ መረጃዎ።
  • ከቤተሰብዎ ውስጥ አብረው ምግብ የሚገዙት፣ የሚያዘጋጁት ወይም የሚያጋሩት እያንዳንዱ አዋቂ ሰው ስም፣ ዕድሜ እና የገቢ መረጃዎች።
  • የቤትዎ ወጪዎች (የማሞቂያ እና የማቀዝቀዣ ወጪዎች፣ የልጆች ድጋፍ፣ የቤት ኪራይ ወይም የቤት መግዣ)።

ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ያመልክቱ


እንደ ፍላጎቶችዎ እና እንደ ሁኔታዎ ለመሰረታዊ ምግብ ለማመልከት ሶስት ቀላል መንገዶች እነሆ፡

ቤተሰብ ከልጆች ጋር

የቤተሰብ ምግብ ሆትላይን

እርስዎ የሚኖሩበት ቤት ውስጥ ልጆች ካሉ (የተደባለቀ የስደት ሁኔታ ያላቸውን ቤተሰቦች ጨምሮ) እና ለማመልከት እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ ለቤተሰብ ምግብ ሆትላይን ይደውሉ። የቋንቋ አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ።

የማህበረሰብ እና ቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች

የጥቅሞች ማዕከል

በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የማህበረሰብ ወይም የቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪ ከሆኑ የመስመር ላይ ቀጠሮ ለማስያዝ የጥቅሞች ማእከል ድረ ገፁን ይጎብኙ። ለመሠረታዊ ምግብ ለማመልከት ሊረዱዎት ይችላሉ።

በራስዎ ማመልከት
ከፈለጉ

WashingtonConnection.org

እርዳታ የማይፈልጉ ከሆነ እና ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) በራስዎ ለማመልከት ከፈለጉ በዋሽንግተን የግንኙነት ጣቢያ በኩል ማመልከቻ በመሙላት ይህንን ማድረግ ይችላሉ።


ካመለከቱ በኋላ


ለቤዚክ ፉድ (Basic Food) ካመለከቱ በኋላ የቤዚክ ፉድ (Basic Food) ቃለመጠይቅን ለማጠናቀቅ ወደ ዋሽንግተን ማህበራዊና ጤና አገልግሎት መምሪያ (Washington Department of Social and Health Services (DSHS)) መደወል ያስፈልግዎታል። ከስቴት በዓላት በስተቀር ከሰኞ-አርብ ከጠዋት 8:00 እስከ ከሰአት 3:00 ድረስ በ877-501-2233 ወደ DSHS መደወል ይችላሉ።

ማመልከቻዎን ካመለከቱ በ30 ቀናት ውስጥ ይህንን ማድረግ አለብዎ። DSHS አይደውልልዎትም።

ጠዋት ላይ እንዲደውሉ እንመክራለን።


ተደጋጋሚ ጥያቄዎች


የቤዚክ ፉድ (Basic Food) ጥቅሞቼ ምን ያህል እንደሚሆኑ መገመት እችላለሁን?

አዎ፣ (ከፍተኛ ያልሆነ) ጥቅማጥቅሞችዎን በDSHS የግምት ድረገጽ ላይ መገመት ይችላሉ፣ እዚህ፡ https://www.dshs.wa.gov/sites/default/files/ESA/csd/documents/bfcalculator/ bf_benefit_estimator.htm