የምግብ አቅርቦት

United Way of King County ከ King ካውንቲ የምግብ ባንኮች፣ Safeway እና DoorDash ጋር በመተባበር የምግብ/መጠጥ እቃዎችን በነጻ፣ በየሳምንቱ በመኖሪያ ቤት ያቀርባል።

ከተመዘገቡ በኋላ በሁለት ቀናት ውስጥ ከእኛ የመረጃ መስጫ ኢሜይል ይደርስዎታል። ይህን አገልግሎት ለተመለከቱ ጥያቄዎች እባክዎ በስልክ ቁጥር 253.237.2019 ወይም በኢሜይል fooddelivery@uwkc.org ያነጋግሩን።.


አቅርቦቱየሚሰራው እንዴትነው


storage room with a conveyor belt containing several boxes with groceries

1. የአስፈላጊ ምግቦች/መጠጦች ሳጥን ወይም ለባህል ተገቢ ምግቦች ከረጢት በአቅራቢያ በሚገኘው የምግብ ባንክ ወይም የምግብ/መጠጥ ማከፋፈያ ይዘጋጃሉ።

person wearing a Live United shirt loads a container of groceries into the trunk of a doordash car

2. የDoorDash ሹፌር (ዳሸር) ምግቡን ሄዶ ይረከባል።

close up of a person organizing a box of canned foods

3. የDoorDash ሹፌሩ (ዳሸሩ) በእያንዳንዱ ሳምንት ያለ ምንም ግንኙነት አቅርቦት ምግቡን በመኖሪያ ቤትዎ ያስረክብዎታል።

ይህ ነጻ አገልግሎት ለማንኛውም ምግብ/መጠጥ የመግዛት አቅም ለሌለው እና የአካባቢውን የምግብ ባንክ ማግኘት ላልቻለ የ King ካውንቲ ነዋሪ ይቀርባል። 

የዜግነት ወይም ስደተኝነት ደረጃዎ ምንም ይሁን ምን በዚህ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ይችላሉ። በምዝገባ ወቅት ምንም የዜግነት ደረጃን የተመለከተ መረጃ አይሰበሰብም። 

እባክዎ ይገንዘቡ: በ King ካውንቲ ውስጥ በሚገኙ በአንዳንድ ቦታዎች ይህ ፕሮግራም ገና በዝግጅት ላይ በመሆኑ ምግቦች/መጠጦችን መቀበል ለመጀመር ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ሊወስድበት ይችላል። 

ምግብ ለማግኘት አስቸኳይ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ ወደ 2-1-1 ይደውሉ። 

ከተመዘገቡ በኋላ በእያንዳንዱ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተጠባባቂነት ደረጃዎን የተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ይደርስዎታል። በተጨማሪም ጥያቄዎች ካሉዎ ወይም የተጠባባቂነት ደረጃዎን ለማረጋገጥ በየትኛውም ጊዜ ቡድናችንን በስልክ ቁጥር 253.237.2019 በመደወል ወይም በኢሜይል fooddelivery@uwkc.org ማነጋገር ይችላሉ።.


ተደጋግመው የሚጠየቁጥያቄዎች


በዚህ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ብቁ የሚሆነው ማን ነው?

በዚህ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ:

  • King County, Washington ነዋሪ መሆን አለብዎ
  • የአካባቢዎን የምግብ ባንክ በአካል ማግኘት ያልቻሉ መሆን አለበት
  • የምግብ/መጠጥ እቃዎችን የመግዛት አቅም የሌሉዎ መሆን አለብዎ

የትኛውም እነዚህን መስፈርቶች አሟላለሁ የሚል ግለሰብ ወይም ቤተሰብ የዜግነት ወይም የስደተኝነት ደረጃው ምንም ይሁን ምን ይህን አገልግሎት ለማግኘት ብቁ ነው። በምዝገባ ወቅት ምንም የዜግነት ደረጃን የተመለከተ መረጃ አይሰበሰብም።

ፕሮግራሙ የሚሰራው እንዴት ነው? ስለ አቅርቦቴ የተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ማግኘት እችላለሁ?

ከመጀመሪያ የምግብ/መጠጥ አቅርቦትዎ በፊት ከቡድናችን መካከል የተወሰነ ሰው ስለ አቅርቦቱ መመሪያዎች ለመጠየቅ እና የግንኙነት መረጃዎን ለማረጋገጥ እርስዎን ያነጋግርዎታል። በየሳምንቱ የምግብ/መጠጥ አቅርቦትዎን የሚጠብቁበትን ቀንና ሰዐት እናሳውቅዎታለን።

በየሳምንቱ የአቅርቦቱ ሹፌር (ዳሸር) በየሳምንቱ የምግብ/መጠጥ አቅርቦትዎን በቅርበት ከሚገኘው የምግብ ባንክ ወይም የምግብ አቅርቦት አጋር ይረከብ እና ያለ ምንም ግንኙነት ማድረግ ከውጭ በራፍዎ ላይ ያስቀምጥልዎታል። የሞባይል ቁጥርዎን ከሰጡ ዳሸርዎ በሚመደብበት ወቅት፣ የምግብ/መጠጥ አቅርቦትዎችዎን የሚወስዱበት ጊዜ እና የምግብ/መጠጥ አቅርቦትዎችዎ መቼ በራፍዎ ላይ እንደሚቀመጡ የተመለከተ የጽሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል። 

ምን የምግብ/መጠጥ እቃዎች እቀበላለሁ?

በአካባቢ ከሚገኙ የምግብ ባንኮችና የምግብ/መጠጥ ማማፋፈያዎች የተለያዩ በቅድሚያ የተዘጋጁ የምግብ ሳጥኖች ሊቀርቡልዎ ይችላሉ። ይህ የታሸጉ ምግቦችን፣ የታሸጉ ፍራፍሬዎችና አትክልትን፣ ፓስታና ሌሎች የተለያዩ የምግብ እቃዎችን ሊይዝ ይችላል። አብዛኞቹ አቅርቦቶች እንደ ዳቦ፣ ወተት ወይም የወተት ተዋጽኦዎች ያሉ የሚበላሹ የምግብ እቃዎች ናቸው። 

የአመጋገብ ገደቦች ካሉብኝ ምን አደርጋለሁ?

የአመጋገብ ገደቦች ወይም አለርጂዎች ካሉብዎ እባክዎ ይህን በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ ያመልክቱ። ከቡድናችን መካከል የተወሰነ ሰው መረጃ ለመሰብሰብ ያነጋግርዎታል። ምንም እንኳን ፕሮግራማችን በአሁኑ ወቅት እያንዳንዱን የአመጋገብ ገደቦች ስለማሟላቱ ማረጋገጫ መስጠት ባንችልም ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። 

የምግብ/መጠጥ አቅርቦቶቼ ባይደርሱኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?

ሁሉም አቅርቦት ደህንነቱ በተጠበቀና በአስተማማኝ መልኩ እንደሚደርስዎ እና ዳሸርዎ ይሁን ማድረጉን ለማረጋገጥ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን! ሆኖም አልፎ አልፎ ስህተቶች ይፈጠራሉ። መደበኛ አቅርቦትዎ የማይደርስዎ ከሆነ በመጀመሪያ በአቅራቢያዎ ማግኘት ስለመቻልዎ ያረጋግጡ። የአፓርታማ ነዋሪ ከሆኑ ከአዳራሽዎ፣ ሎቢዎ፣ መግቢያዎ ወይም ሌሎች የጋራ መገልገያ ቦታዎች ያረጋግጡ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ነዋሪ ከሆኑ አቅርቦቱ በራፍዎ፣ ማሽከርከሪያ መንገድዎ ወይም በመልእክት ሳጥንዎ ያልቀረበልዎ ስለመሆኑ ያረጋግጡ።

እነዚህን ሁሉ ደረጃዎች ከወሰዱ በኋላ ምግብዎን ፈልገው ማግኘት ካልቻሉ እባክዎ ወዲያውኑ ያሳውቁን። ችግርዎን የምንፈታበት የተሻለ እድል ለማግኘት እንዲያስችለን በአስቸኳይ ለቡድናችን በስልክ ቁጥር 253.237.2019 ይደውሉ ወይም በኢሜይል fooddelivery@uwkc.org መልዕክት ይጻፉ።

በዳሸሬ ላይ ችግር ካለብኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

እባክዎ ችግርዎን በአስቸኳይ ለመፍታት ይረዳን ዘንድ ቡድናችንን በስልክ ቁጥር 253.237.2019 በመደወል ወይም በኢሜይል fooddelivery@uwkc.org ያነጋግሩ።

አቅርቦቶች መቀበሌን ማቆም እፈልጋለሁ። ይህን እንዴት መምረጥ እችላለሁ?

ለቡድናችን በስልክ ቁጥር 253.237.2019 ይደውሉ ወይም fooddelivery@uwkc.org ኢሜይል ያድርጉ።. 

የ King ካውንቲ ነዋሪ አይደለሁም። በማህበረሰቤ ውስጥ ተመሳሳይ ፕሮግራም አለ?

ይህ አገልግሎት የሚቀርበው ለ King ካውንቲ ነዋሪዎች ብቻ ቢሆንም የምግብ ባንኮችና የምግብ ፕሮግራሞች በመላው ዋሽንግተን ግዛት ውስጥ መስራታቸውን ይቀጥላሉ። በማህበረሰብዎ ውስጥ ስላሉ አገልግሎቶች የተመለከተ መረጃ ለማግኘት ወደ 2-1-1 ይደውሉ።


ስፖንሰር አድራጊ:

sponsor logo block for Door Dash program